የሐረር መቻቻልና ሌሎች መጣጥፎች

Books Ayoub Abdullahi 747 10th Nov, 2020

Embed

Loading please wait...

Overview

መግቢያ ይህ መጽሃፍ በተለያየ ግዜ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ የተጻፉ የተተነተኑ ና የተሄሱ ራእዮች ምኞቶችና ሀረርና ሀረሪን ጉዳይ መከላከሎችና ተማጽኖዎችን ያካተቱ ጽሁፎችን ያጠቃልላል፡፡ የመጀመሪያው የሀረር ሰላምና መቻቻል ተሞክሮ የሚለው በጥናት ላይ የተመረኮዘ ጽሁፍ ሲሆን በ4 አገር አቀፍ መድረኮችና በአንድ ክልላዊ መድረክ ቀርቦ መልካም የሆነ ግብረ መልስ የተገኘበት ነው፡፡ ሆኖም ጽኁፉ አሁን የመታተም እድል ሲያገኝ፤ ምንም እንኳን ምርምር ስራ በወቅት የተገደበ ቢሆንም ዘላለማዊ ስለማይሆን አሁናዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣሙ ጉዳዮች በመግጠማቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ በቅንፍ አስተያየት በመጨመር ካለው ነባራዊ ሁኔታጋር ለማጣጣም ተሞክሯል፡፡ በመሆኑም አንባቢ ይህን ሁኔታ በዝህ ደርዝ ተገንዝቦ ልመለከተው እንደሚያስፈልግ አደራ ለማለት ደራሲው ይወዳል፡፡ ያልተነገረላቸው ወይም ካልተጻፈላቸው ሰዎች መሀል የከቢር ጃሚዕን አውቶ ባዮግራፊ ወጣቱ ትውልድ የዓላማ ጽናትን ጥበብን እንዲማርባቸው ለአብነት ቀርቦኣል፡፡ ሌሎች ጽሁፎችን ስንመለከት ደግሞ የሀረሪ ህዝብ የእርቅ ስርዓት፤በይቅርታ እንሻገር በፍቅር እንደመር የመተግበር ቀን በሚል ጽሁፍ ላይ የተሰጠ የግል አስተያየት፤ የሎሳንጀለስዋ ገዢ ማስታወሻ፤ የእህትማማች ከተሞች፤ የሙስሊሞች ጉዳይ ከሐረሪዎች ምን ጉዳይ አለው፤ የሀረሪ ቋንቋ ታሪካዊ ሂደት፤ ሀረሪ መሰረታዊ ጉዳች ላይ ለውጥ ማካሄድ፤ ህያውቷ ሙዝየምና ስጋቷ የሚሉና እንድሁ ደራሲው የራሱን አመለካከትና ምኞት ያንጸባረቀባቸው መጣጥፎች የቀረበበት ስለሆነ አንባቢው ግዜውን ሰጥቶ ቢያነብልኝ ቁም ነገር እንደሚቀስሚበት እንደሚዝናናበት እንድሁም ትክክለኛውን ሁኔታ በጉዳዩ ላይ ያስረዳሉ ብዬ ስለማስብ መልካም ንባብ እያልኩ እጋብዛለሁ፡፡ ከጻሃፊው

Please Log in to comment

Harari E-Book Share is a website where you can store any eBook online for easy sharing. The idea behind the site is to make it more convenient for people to share large amounts of eBooks online.