
የሀረሪ ታሪካዊ ጽሁፎች መድብል
...በአርባ አምስት ርእሶች በአርባውበአማረኛ ስጻፉ አምስቱ ብቻ በሀረሪ ቋንቋ የተጸፉ ናቸው፤ ከ10 ክፍሎች አንዱና ዘጠነኛው አምስት የተለያዩ ጽሁፎች ወይም
የሀረር ኢኮኖሚ የተወሰኑ ገፅታዎች ምርምር እና የሀረር አሚሮች (1825-1875 እ.ኤ.አ) የቤተሰብ ምጣኔ ሐብት ምዝገባ ሪኮርድ ተርጓሚው አቶ ዩሱፍ አህመድ ይህን ጽሑፋቸውን ለማቅረብ ልዩ ጥረት ለማድረጋቸው ጽሑፉ ራሱ ምስክር ነው፡፡፡ በዘመኑ የነበሩ ተጓዦችና ታሪክ ፀሐፊዎች መጻሕፍት በማገላበጥ ፤ እንደዚሁም ከታሪክ አዋቂዎች ጭምር መረጃ በማሰባሰብ እና ምክር በመቀበል ጽሑፉን በማበልፀግ የተሟላ ለማድረግ በእጅጉ ጥረዋል፡፡ አንዱ አሳንሶ ወይም አጉልቶ ያቀረበውን ከሌላው ጋር፤ ሌላው ያላነሳውን እና ያልጠቀሰውን ካወሳው ጋር በማመሳከር ጽሑፉ ተቀነባብሮ እና በመረጃዎች ተሟልቶ የቀረበ በመሆኑ በጣም ተመስጨበታለሁ፡፡ በተለይ በጥንታዊ የእጅ ጽሑፉ (በእጅ ጽሑፍ ሰነድ) ላይ የተሰጠውን ትንታኔም ሆነ በየዘመኑ የነበረውን የመረጃ አያያዝ ችሎታ ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ አተረጓጎሙን አስመልክቶ በቃላት አመራረጥም ሆነ በዓረፍተ ነገር አሰካኩ ይዘቱን በግልፅ ለማስተላለፍና የአቀራረብ ስልቱንም ለማንፀባረቅ ተጥሯል፡፡ ጽሑፉ በየመስኩ ጠቃሚ እውቀት በስፋት የሚቀሰምበት እንደመሆኑ ጽሑፉን ማንበብ ጠቀሜታው የጎላ ነው ፡፡ ዓሊ ዩሱፍ ዓሊ ኬነዋቅ